News and Events
ሲዲኦ /CDO/ ግብረ ሰናይ ድርጅት በወረዳውና በክፍለ ከተማው በጤናው ዘርፍ ያከናወናቸው ስራዎች ላይ ከባለ ድርሻ አጋር አካላት ጋር የልምድ ልውውጥ ማካሄድ ጀመረ 2025-12-28 08:29:41 |
| ሲዲኦ /CDO/ ግብረ ሰናይ ድርጅት በወረዳውና በክፍለ ከተማው በጤናው ዘርፍ ያከናወናቸው ስራዎች ላይ ከባለ ድርሻ አጋር አካላት ጋር የልምድ ልውውጥ ማካሄድ ጀመረ። ጫጫ፤ ታህሳስ 15 ቀን 2018 ዓ.ም (አጠመኮጉ)፦ \r\nሲዲኦ /CDO/ ግብረ ሰናይ ድርጅት በወረዳውና በክፍለ ከተማው በጤናው ዘርፍ ያከናወናቸው ስራዎች ላይ ከባለ ድርሻ አጋር አካላት ጋር የልምድ ልውውጥ ማካሄድ ጀምሯል። Collaborative Development organization /CDO/ የተባለው ልማታዊ ግብረ ሰናይ ድርጅት በአንጎለላና ጠራ ወረዳ ኮቱ እና በደብረ ብርሃን ሪጂኦ ፖሊታን ከተማ አስተዳደር ጫጫ ክፍለ ከተማ ባሉ ሁለት ጤና ጣቢያዎች የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል ማህበራዊ ኃላፊነትን /ተጠያቂነትን መወጣት ላይ አተኩሮ ይሰራል፤ በዚህ ልምድ ልውውጥ ግብረ ሰናይ ድርጅቱ ከጤና ጽ/ቤቶቹ ጋር በመተባበር ያለፈውን አንድ ዓመት በተቌማቱ ከመንግስትና ከማህበረሰቡ ጋር በቅንጅት ያከናወናቸውን ተግባራት ሌሎች ግብረ ሰናይ ድርጅቶችንና የመንግስት አካላትን በመጋበዝ የትውውቅ እና የውይይት መድረክ በዛሬው ዕለት በማካሄድ ጀምሯል። በዛሬው ዕለትም የድርጅቱ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ሞገስ የአንድ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበው ከአጋር አካላቱ ጋር ውይይት ተካሂዷል።በነገው ዕለትም ተጋባዥ ባለድርሻ አካላቱ በመስክ ተገኝተው በተግባር የተሰሩ ተግባራትን በመጎብኘት ልምድ ልውውጡ እንዲካሄድ እንደሚደረግ ተገልፆል። |
![]() ![]() ![]() ![]() ![]() ![]() ![]() ![]() |







